"The Nothing About Us Without Us Act: WA HB 1802", produced by Rooted in Rights - Amharic transcript የድምጽ ዝርዝር፡ የአካል ጉዳተኞች የመብት ተሟጋቾች በቪዲዮ የስልክ ጥሪ ስለ ያለእኛ ስለእኛ መወራት የለበትም ህግ (Nothing About US Without Us bill) ሃሳባቸው አጋርተውናል። - ያለእኛ ስለእኛ መወራት የለበትም ህግ (Nothing About US Without Us bill) እኛ አካል ጉዳተኞች እንደ አካል ጉዳተኛ ዜጎችነታችን እኛን የሚመልከቱ የፖሊሲ ውሳኔዎች የሚመለከቱ እያንዳንዱ ግብረ-ሃይሎች፣ የስራ ቡድኖች፣ እና ኮሜቴዎች ውስጥ ሙሉ በሙሉ እንድንወከል ያደርጋል። - ይህም በጣም ጠቃሚ ነው ምክኒያቱም ብዙ ህጎች፣ ብዙ መመሪያዎች፣ እኛን ሳያሳትፉ አልፈዋል። - የአካል ጉዳት የሌለባቸው በህግ አውጪ ቦታ ላይ ያሉ እና የስቴት ሃላፊዎች በቅጽበት እኛ የሚያስፈልገንን ያውቃሉ ብለን አንጠብቅም። - እየኖርነው ስለሆነ ከእኛ በላይ ስለእዚህ ጉዳይ ለመናገር ትክክለኞቹ ሰዎች ነን። - ህግ አውጪዎቼን ብዙ ጊዜ እንደሚከተለው ብያቸዋለሁ፣ “እዚህ አለሁልዎት፣ እኔን አናግሩኝ፣ እናንተን ልረዳ ነው እዚህ ያለሁት።” - በታሪክ ሲታይ፣ እኛ በሌለንበት ጊዜ፣ ብዙ መጥፎ ፖሊሲ ይወጣል። በግድ ተቋምን ማቋቋም፣ በግድ መካንነትን መፈጸም፣ የአካል ጉዳተኞች ጠይቀውት የማያውቁት ነገር ግን ብዙ ሃይል እና ቁጥጥር በአካል ጉዳተኞች ላይ ይፈጸማል። - ጊዜው አሁን ነው... እነዚህ ህጎች ሲረቀቁ እኛ መሳተፍ ያለብን ጊዜ ድሮ ቢሆንም አሁንም ቢሆን መሳተፍ አለብን። - ...ምክኒያቱም ያኔ እና ያኔ ብቻ ነው ሰብአዊ መብቶቻችንን የሚያስጠብቅ ህግ እንዲወጣ በማድረግ ልዩነት ማምጣት የምንችለው... - ... እናም በጥሩ አላማ የተደረጉ ጥረቶች ከአላማ ውጪ የሆነ ጉዳት እንዳያመጡ መከላከል የምንችለው ያኔ ነው። - የተሻለ ህግን አሁን ማውጣት ይቻላል ብዬ አስባለሁ ምክኒያቱም ከተለያየ አመጣጥ የመጡ እና የተለያየ የአካል ጉዳት ያለባቸው ሰዎች ሃስብ ይካተታል። - So Nothing About Us Without Us is where equity begins. ስለዚህ ያለእኛ ስለእኛ መወራት የለበትም ህግ (Nothing About US Without Us bill) እኩልነት የሚጀምርበት ቦታ ነው። End of transcript.